ኢት-ኢኮኖሚ ET- ECONOMY የህወሃት የጦር አበጋዞች
ፀ/ት ፂዬን ዘማርያም)
የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (Metals and Engineering Corporation (METEC)
TPLF is the root cause of all our problems, Remove TPLFበመከላከያ ሚኒስትር ስር የሚገኘው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ/ሜቴክ)፣ ሲጀምር አስራሁለት የሚደርሱ የተለያዩ ከደርግ/ወታደራዊው መንግስት በተወረሱ ፋብሪካዎችን ሥራ የጀመረ ድርጅት ነው፡፡ ሜቴክ በ2010 እ.ኤ.አ በአስር ቢሊዩን (10,000,000,000) ብር መነሻ ካፒታል የተመሠረተ ድርጅት ነው። በአሁኑ ግዜ በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ዘመን ከ75 ፋብሪካዎች በላይ ያሰባሰበ ድርጅት ለመሆን ችሏል። ሜቴክ ኮርፖሬሽን ከ13,000 ሠራተኞች ሲኖሩት ከነዚህ ውስጥ 1,000 ዎቹ ማሃንዲሶች ናቸው።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሃገሪቱን የኢኮኖሚ ትስስር መሪ ዶክተር ደብረፂዋን ገብረሚካኤል ሜቴክ በሃገር ውስጥና ከባህር ማዶ ሃገራት የቢዝነስ አጋሮቹ ጋር በመሆን ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ምርትና ሸቀጦችን በመተካት የውጭ ምንዛሪ ለማዳን ሜቴክ ይንቀሳቀሳል ቢሉም ሜቴክ የሰራው ምርትና ያዳነው የውጭ ምንዛሪ ደፍረው አልገለፁም። ሜቴክ መንግስታዊ ሞኖፖሊ እንደሆነ የግሉን ዘርፍ ስራ እየነጠቀ እንደሆነ ዶክተሩ የሚመሩት ቴሌኮም ከዓለማችን ካሉ ሃገራት የመጨረሻ ተርታ ውስጥ መሆኑን መረዳት የተሳናቸው ኢንተርኔት አጠቃቀም ባለመቻላቸው ነው ተብለው ይታማሉ፡፡
ከህወሃት የጦር አበጋዞች ሜቴክን የሚመሩት ጀነራል ማኔጀር ብርጌደር ጀነራል ክንፉ ዳኘው ሲሆኑ እንዲሁም ምክትል ጀነራል ማኔጀር ኮለኔል ጠና ኩርንዲ (Tena Kurnde (Col.) ይባላሉ። በመከላከያ ሚኒስትር ስር የሚገኘው፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) በማስተዳደር ላይ ይገኛሉ። ሜቴክ በኢትዩጵያ ኢኮኖሚ ዘርፎች በሲቪልና በወታደራዊ መስኮች፣ ያለ ሕግ የሚንቀሳቀስ የህወሃት የንግድ ካንፓኒ ሲሆን፣ የግሉን ዘርፍ ያገለለና የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ወደ ዕዝ ኢኮኖሚ የመለሰ ስርዓት መሆኑንና ከደርግ ስርአት ውድቀት መማር ያልቻለ፣ ለማንም ህሊና ላለው ዜጋ ሁሉ ግልጽ ነው። የሃገራችንን ኢንደስትሪ /መኑፋክቸሪንግ/ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ቀስ በቀስ ድጋፍ ከተደረገላቸው ማደግ ይችላሉ። በልማታዊ መንግስታት በቻይና፣ ደቡብ ኮሪያና፣ ታይዋን በመሳሰሉት ሀገራቶች በኢንደስትሪ /መኑፋክቸሪንግ/ ዘርፍ በተሰማሩ በሲቨሉ ህብረተሰብ እውቀትና ስልጠናና በመንግስት ድጋፍ የኢንደስትሪ ዘርፍ አድጓል። የህወሃት ልማታዊ መንግስት በመከላከያ ሚኒስትር ስር በተገነባው፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሃገሪቶ የኢንደስትሪ ዘርፍ እድገት በምንም ተዓምር አታመጣም። የግሉን ዘርፍ ደፍጥጦ በመከላከያ ሠራዊት የኢንደስትሪ አይገነባም። በሌሎች ሃገራትም በዚህ መንገድ የተገኘ የኢኮኖሚ እድገትና ግኝት የለም። የህወሃት የጦር አበጋዞች፣ ጀነራል መኮንኖቹ በአዲስ አበባና በየክልሎቹ ከተሞች ፎቆች የሚገነቡት ዋነኛ የገንዘብ ምንጭ በመሆን የምትታለበዋ ላም ሜቴክ መሆኖ ያደባባይ ሚስጢር ነው። በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ፣ ከደርግ መንግስት ለህወሃት መንግስት “የማፍያ መንግስታዊ ሞኖፖሊ” የህዝብ ኃብትን የወረሰና ያሸጋገረ፣ የእዝ መንግስታዊ ኢኮኖሚ የዘረጋ መሆኑን፣ የዓለም ባንክ ያወቀው፣ አይኤም ኤፍ የሞቀው፣ በእውቀት የላቁት፣ የአውሮፓና አሜሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ ጠበብት የሚያውቁት ሃቅ ነው።
1986 እ.ኤ.አ. በመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ተቆቁሞ በወታደራዊው መንግስት ከግለስብ ኢንቨስተሮች የወረሰውን 365 መንግስታዊ ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፍ አዘዋውራለሁ ቢልም አሰራሩ መልሶ፣ ከደርግ ወደ ህወሃት መንግስታዊ ኃብትነት በማዘዋወር የሚዘወር መንግስታዊ ሞኖፖሊ ነው። የደርግና የህወሃት መንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ የካፒታሊስቱን ነፃ ገበያ ኢኮኖሚ በመተው፣ መንግስታዊ ሞኖፖሊ በመፍጠር አገሪቷን ወደ እዝ ኢካኖሚ ከተዋታል። የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስታዊ የልማት ድርጅቶችና የገዥው ፓርቲ የንግድ ድርጅቶች የአገሪቱን ኢኮኖሚ ዘርፎች ተቆጣጥረውታል። መንግስታዊ ሞኖፖሊ በቴሌካምኒኬሽን፣ በኤሌትሪክ ኃይል፣ በባንክ፣ በኢንሹራንስ፣ በአየር ትራንስፖርት፣ በመርከብ መጓጓዣ፣ የስካኳር ፋብሪካዎች፣ እርሻዎችና የመሬት ኃብት በመንግስታዊ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። የሃገሪቱ የሲሚንቶ ዘርፍ፣ የትራንስፖርትና የጭነት መጓጓዣዎች፣ የማዳበሪያ ፋብሪካና የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች በአመዛኙ በመንግስት፣ በኢፈርት፣ ሜቴክና ሜድሮክ ኃብት ናቸው።
መንግስታዊ ሞኖፖሊ የግሉን ዘርፍ ኢኮኖሚ በማቀጨጭና በማቆርቆዝ ላይ ይገኛሉ። ነፃ ገበያ ባለመኖሩና የተመቻቸ የገበያ ውድድር ህግ ባለመኖሩ፣ የመንግስት ቢሮክራሲ የህግ ደንብና አፈፃፀም በግሉ ዘርፍ ላይ ከሚፈፀሙ አድሎዎች መኃል ለመጥቀስ
(1) ከባንክ ብድር የማግኘት ዕድል፣ ለኢፈርት፣ ሜቴክ፣ ሜድሮክ የመሳሰሉ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚያበድረው ብድር አድሎ የተሞላበት ነው። በጀነራል ፃድቃን ገብረ ትንሳይ ለተቆቆመው ራያ ቢራ ፋብሪካ ባንኩ 910 ሚሊዩን ብር እንዲያበድር ቀጭን ትእዛዝ ተሰጥቶ ተበድረዋል።
(2) ፈጣንና ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎት የማግኘት እድል
(3) የውጭ ምንዛሪ በቅድሚያ የማግኘት እድል
(4) የመንግስት ጨረታን ያለውድድር የማግኘት እድል
(5) የሃገር ውስጥና የውጭ ገበያ የማግኘት እድል
(6) የመሬት ጥያቄ ለመንግስትና ለግሉ ዘርፍ ለተሰማሩ አድሎ መኖር
(7) የመንግስት ግብር በመንግስታዊና በግሉ ዘርፎች ያለ ልዩነት
(8) በብሔራዊ ባጀት “የመንግስት የልማት ድርጁቶች” አጠቃላይ ባጀት ይገለፃል እንጂ የተናጥል ባጀታቸው ለህዝብ ይፋ አለመደረግ፣ እንዲሁም የኦዲት ሪፖርት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በስተቀር የሌሎቹ “መንግስታዊ ልማት ድርጅቶች” ተደርጎ አይታወቅም።
እነዚህ ድርጅቶችን በቦርድ የሚያስተዳድሩት የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ሹማምንቶች፣ የፖለቲካ ካድሬዎችና የጦር ጀነራል መኮንኖች ሲሆኑ በትምህርትና በእውቀት ነፃ ውድድር የተያዘ ሥራ ባለመሆኑ ብዙዎቹ ለኪሳራ ይዳረጋሉ።
በኢትዮጵያና ሌሎች ታዳጊ አገሮች ውስጥ የመንግስት ልማት ኢንተርፕራይዝና ኮርፖሬሽኖችን ንብረቶች ወደ ግሉ ዘርፍ መተላለፍና መሸጥ ዋነኛ ምክንያቶች፣ የገንዘብ አያያዝ ብክነትና ሙስና በየግዜው እየጨመረ መሄድ፣ ንብረቶቹን የማስተዳደር ብቃት ደካማነት በዚህም ምክንያት በየአመቱ የመንግስት ድጎማ እየተደረገላቸው በኪሳራ መስራታቸው ነው። የመንግስታዊ ፋብሪካዎች አስተዳደራዊ ስርዓት በዘመዳ ዘመድ ሥራዎች መጠመድ፣ በሙስና መጨማለቅና ነፃ የገበያ ስርዓት በመክላት ሃገሪቱን ወደ እዝ ኢኮኖሚ በመዝፈቅ፣ ኢኮኖሚያዊ ፍልስፍና አልባ የማፍያ ስርዓት ዛሬም ተክለዋል።
ከወታደራዊ መንግስት ንብረትነት ወደ ህወሃት መንግስት ንብረትነት ሽግግር በፕራይቨታይዜሽን ስም የተሸጋገሩ በተለይ፣ የመከላከያ ሠራዊቱና የደህንነት ከፍተኛ ሹማምንቶች በተለይ ጀነራል መኮንኖቹና ሹማምንቱ በመለስ ዜናዊ ፍልስፍና ሠራዊቱ ለህወሃት መንግስት ታማኝ ሆኖ እንዲቀጥል በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች በመግዛት፣ መኖሪያ ቤት፣ ሁለት ሦስት መሬትቶች እንዲሸጡና ቤት እንዲሰሩ በማመቻቸት፤ ከአንድም ሁለት ሦስት መኪኖች ለቤተሰባቸው መጠቀሚያ ጭምር በመስጠት፣ ሲታመሙ ውጭ ሃገር ልኮ በማሳከም፣ ለበታች ሹማምንቶችም ኮንዶሚኒም ቤቶች ገንብቶ በመስጠትና የቤት መስሪያ ቦታ በመስጠት ይደልላሉ። በወታደራዊ መንግስት ከግለሰብ ኢንቨስተሮች የተወረሱትን ንብረቶች ወደ ሕወሃት መንግስት ንብረትነት በማሸጋገር የሜቴክ ዓይነት ድርጅቶች በማቆቆም የህወሃት ጀነራል መኮንኖችና ሹማምንቶችን በንግዱ ዓለም በማስመጥ፣ በሙስና በማጥመቅ፣ በዘመዳ ዘመድ በመጠቃቀም፣ ህዝቡን አፍኖ በመግዛት የስልጣን መንበራቸውን ማስጠበቅ ዋነኛ ዓለማቸው ነው። ከነዚህ “መንግስታዊ የልማት ድርጅቶች” ውስጥ በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የመከላከያ ሚኒስትር ስር በተቋቋመው፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ስም ያለአንዳች ጨረታ የተወረሱ ዋና ዋናዎቹ የህዝብ ኃብቶች ቀጥሎ በዝርዝር ይቀርባሉ፡፡
(1) የደጀን አቨየሽን ኢንጂነሪንግ ኮምፕሌክስ (Dejen Aviation Engineering Complex (DAVEC)
በወታደራዊው መንግስት በ1984 እ.ኤ.አ. በኢትዮጵያ አየር ኃይል የተመሠረተው የአውሮፕላን ማደሻና መመርመሪያ ማዕከል በመሆን ከፍተኛ የአየር ኃይል አውሮፕላን ጥገናና እድሳት ሥራ በማድረግ ይታወቃል። በ2010 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ዘመን ድርጅቱ ዳቦ ሳይቆረስ ደጀን አቨየሽን ኢንድስትሪ (Dejen Aviation Industry (DAVI)) ተብሎ በ(ብኢኮ) ንብረት ሆኖ ተወረሰ። ከአዲስ አበባ 47 ኪሎ ሜትር ርቀት በደብረዘይት ከተማ የሚገኘው ኢንደስትሪ በስሩ፣ ስምንት ፋብሪካዎች በማደራጀት የማይንቀሳቀስና ተንቀሳቃሽ የአውሮፕላን ክንፍ ማምረቻ ፋብሪካዎች፣ ኤሮስፓስና ሜካኒካል ፋብሪካ፣ አቪዩኒክስ ሲስተም ኢንቲግሬሽን ፋብሪካ፣ ፓወር ፕላንት ፋብሪካ፣ የአውሮፕላን አካልና መቃን አቆም /ስትራክቸር ፋብሪካ፣ ዩኤቪ ምርቶች ፋብሪካና የአውሮፕላን ጥራትና ችሎታ መፈተሻ ማዕከል ፋብሪካዎችን ያካትታል። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሌተናል ኮነሬል ኪዱ ፀጋዬ እና ሜጀር ሃይለ ገብረ ጊዮርጊስ እንደሆኑ ይታወቃል።
(2) የጋፋት ኢንጂነሪንግ ፋብሪካ (Gafat Engineering Factory)
በወታደራዊው መንግስት በ1989 እ.ኤ.አ. ኤኬ-47 እና አርፒጂ ቀላል መትረየስ ጠመንጃ በማምረት ይታወቃል። በ2002 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ዘመን ካንፓኒው ስሙን በመቀየር ጋፋት የመሳሪያ ኢንደስትሪ (Gafat Armament Industry) በመባል የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ። ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ደቡብ ምስራቅ 65 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ሲገኝ፣ ፋብሪካው በ4,412 ስኮየር ኪሎሜትር ቦታ ላይ የተገነባ ነበር።፡ፋብሪካው በተጨማሪ ኤኬ 103፣ 40 ሚሊሜትር የቦንብ አውዘግዛጊና ሌሎች አቶማቲክ መሣሪያ በጦር መኪናዎችና በሂሊኮፕተር ላይ የሚገጠሙ ላውንቸር፣ ማኑፋክቸሪንግ የጦር መሳሪያ መለዋወጫና ብረት በማቅለጥና ምስል መቅረፅና በመጫን ምርቶችን አምርቶ ለገበያ የማቅረብ አላማ አካቶ ፋብሪካዉ ማምረት ጀመረ። የጋፋት የመሳሪያ ኢንደስትሪ ስድስት ፋብሪካዎችን ያካትታል እነሱም፣ አነስተኛ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ማምረቻ፣ መካከለኛ ካሊበር ማምረቻ ፋብሪካ፣ ሮኬት ላውንቸር እንዲሁም ሞርታርስ ፋብሪካ ማምረቻ እና ከባድ መሳሪያ የመድፍ ማምረቻና ቅርብ ርቀት የሚተኩስ ጠመንጃ ፋብሪካ ማምረቻ ፣ እንዲሁም የመሣሪያ መለዋወጫ ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካዎች ያካትታል። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ግሩም ገብረኪዳንና ሜጀር አፅብሃ ገብሬ እንደሆኑ ይታወቃል።
(3) የናዝሬት የትራክተር መገጣጠሚያ ፋብሪካ (Nazareth Tractor Assembly Plant (NTAP)
በወታደራዊው መንግስት በ1984 እ.ኤ.አ. ከአዲስ አበባ ከተማ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት በናዝሬት ከተማ ውስጥ በ114,388 ስኩየር ሜትር ባታ ላይ የተገነባ ነው። ፋብሪካው ትራክተር በመገጣጠም፣ የውሃ መርጫ ማጠጫ/ፓምፕ እንዲሁም የተለያዩ የግብርና መሣሪያዎች መገጣጠሚያና መለዋወጫ ምርቶች በመስራት ይታወቅ የነበረ ነው። በ2010 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ ኢህአዴግ መንግስት ዘመን ስሙ ተቀይሮ የአዳማ የግብርና ማሽነሪ ኢንደስትሪ (Adama Agricultural Machinery Industry (AAMI) ተብሎ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ። ድርጅቱ የአራት ፋብሪካዎች ስብስብ ነው። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሻንበል ሚኪያስ ሜጋ ይባላሉ።
(4) የናዝሬት የልብስና ጨርቃ ጨርቅ ኢንደስትሪ
በወታደራዊው መንግስት በ1987 እ.ኤ.አ. የልብስና ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ፣ የልብስ መስፍያ ፋብሪካ፣ ፓራሹትና የዕቃ ማንሸራተቻ ፋብሪካ፣ የጫማና የእጅ ጎንት ፋብሪካና የቤት ዕቃዎች ማምረቻ ፋብሪካ የመሳሰሉትን በማምረት ይታወቃል። ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 105 ኪሎ ሜትር ርቀት በናዝሬት ከተማ ውስጥ ይገኛል። በ2010 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ዘመን የአዳማ የልብስ ኢንደስትሪ (Adama Garment Industry (AGI) ተብሎ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ከተማ አብዲ ይባላሉ።
(5) የአቃቂ መሠረታዊ ብረታ ብረት ኢንደስትሪ (Akaki Basic Metals Industry (ABMI)
በወታደራዊው መንግስት በ1989 እ.ኤ.አ. በመባል ልዩ ልዩ ከፍተኛና ዝቅተኛ መገጣጠሚያና ማኑፋክቸር መለዋወጫዎች እንዲሁም የካፒታል ጉድስ ማለትም የስኳር ማምረቻ ወፍጮ ፍብሪካ፣ የስኳር ማቀነባበሪ ማፍያና መቀቀያ መለዋወጫዎች፣ የብረት ኳሶችና የብረት ሠፌዶች፣ የጉድጎድ የብረት ክዳኖችና መቃኖች እና ተንቀሳቃሽ የብረት ዘንጎች በማምረት ይታወቃል። ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት በአቃቂ ከተማ ወጣ ብሎ ይገኛል። በ2010 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ዘመን የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ( Privatization and Public Enterprises Supervising Agency ) አማካኝነት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ጀማል አብዲልከድር እና ሻንበል ሙሳ ይማም ይባላሉ፡፡
(6) የብሸፍቱ አውቶሞቲቨ ኢንደስትሪ (Bishoftu Automotive Industry (BAI)
በኢህአዴግ መንግስት በ1999 እ.ኤ.አ. በብሄራዊ መከላከያ ሚኒስትር አስተዳደር የተመሰረተ ፋብሪካ ነበር። በ2010 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተዘዋወረ። ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 45 ኪሎ ሜትር ርቀት በደብረዘይት ከተማ ውስጥ ይገኛል። ፋብሪካው የህዝብ ትራንስፖርት አውቶብሶች፣ የከተማ ውስጥ አውቶብሶች፣ የጭነት መኪናዎች፣ ፒክ አፕ መኪናዎችና ሲዩቪ መኪኖች ይገጣጥማል። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሌተናል ኮነሬል ገብረ መድህን ገብረ ሥላሴና ሻንበል አብዱልፈታ ናስር ይባላሉ።
(7) የኢትዩጵያ ፕላስቲክ ኢንደስትሪ ( Ethiopia Plastics industry)
በቀ.ኃ.ስ ዘመን በ1960 እ.ኤ.አ. የተገነባው ፋብሪካ ነበር። በ1973 እ.ኤ.አ. በወታደራዊው መንግስት 55 በመቶ የመንግስት ኃብትነትና ቀሪውን 45 በመቶ ለባለቤቱ ድርሻ ንብረትነት በመስጠት ፋብሪካው ቀጠለ። በ1978 እ.ኤ.አ. ፋብሪካውን የደርግ መንግስት ሙሉ በሙሉ ወረሰው። በ2011 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ዳግም ተወረሰ። ፋብሪካው ዋና መስሪያ ቤት በአዲስ አበባ በሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ሲሆን የፋብሪካው ማምረቻ ቦታ በገርጂ ይገኛል። የፋብሪካው ምርቶችም፣ የተለያዩ የፕላስቲክ ምርቶች፣ የሽቦና የኬብል ምርቶች፣ ተጣጣፊና ደረቅ ኮንዲዩቶች፣ ፒፒር እና ኤችዲፒኢ ቱቦዎች/ፓይፖች፣ ፖሊቲሊን ምርቶች ማለትም የፊልም ፓኮዎች፣ ተጣጣፊ መጠቅለያ ሽፋን፣ የገበያ ቦርሳዎች፣ ፖሊቲሊን ቱቦዎች፣ ረዥም የላስቲክ ቱቦ፣ የኢንደስትሪ ቦት ጫማዎች፣እና መገናኛ ሣጥኖች በማምረት ይታወቃል። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ አቶ ጋሻው ይመር ይባላሉ።
(8) ህብረት ማኑፋክቸሪንግና የማሸን ግንባታ ኢንደስትሪ (Hibret Manufacturing and Machine Building Industry)
(HMMBI) በቀ.ኃ.ስ ዘመን በ1945 እ.ኤ.አ. የተገነባው ፋብሪካ ነበር። በ2010 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተወረሰ። ፋብሪካው በአዲስ አበባ በሜቴክ ዋና መስሪያ ቤት አጠገብ ይገኛል። HMMBI has five factories: machine building factory, material treatment and engineering factory, mechanical subsystem factory, precision machinery factory and conventional manufacturing factory. The manufactured products primarily serve as input into a wide variety of industrial machinery used by agencies in the public and private sectors. በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር ተሰማ ግደይ ይባላሉ።
(9) ሃይ-ቴክ ኢንደስትሪ (Hi-Tech Industry (HTI))
በ2011 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተቆቆመ። ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት በለገዳዲ ከተማ ውስጥ ይገኛል። Production and assembly of communication radios (both for military and commercial purposes), various types of radar systems, electronic devices such as TV sets, electromechanical devices such as energy meters, harmonic analyzers, optical devices such as night vision devices, thermal imagers, and security cameras, other electronic technology products. በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር በሪሁ ግደይና ሻንበል ጋሻው ይባላሉ።
(10) ሆሚቾ የጦር መሣሪያ ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ (Homicho Ammunition Engineering Industry(HAEI))
በ1987 እ.ኤ.አ. በወታደራዊው መንግስት ዘመን፣ ፕሮጀክት 130 በመባል የተገነባው ማኑፋክቸሪንግና የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፋብሪካ ሲሆን ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 140 ኪሎ ሜትር ርቀት በምስራቅ ሸዋ ዞን (አንቦ/ጉደር) በ980,000 ስኩየር ሜትር (በ224 ሄክታር) ላይ የተገነባ ፋብሪካ ነበር። ፋብሪካውን የገነቡት የሰሜን ኮሪያና የራሽያ መንግስታቶች በህብረት ነበር። ከዛም በ2010 እ.ኤ.አ. በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ተዘዋወረ። የሰባት ፋብሪካዎች ስብስብ ሲሆን እነሱም የአነስተኛና መካከለኛ የጦር መሣሪያ ማምረቻ፣ ከፍተኛ የጦር መሣሪያ ማምረቻ ግምጃ ቤት ፋብሪካ፣ የሣጥንና የመርከብ ጥገና፣ የፈንጂና የሚሽከረከር/ውልብልቢት ማምረቻ፣ የሮኬት ማምረቻ፣ ባልቦላ ወይም የመብራት ቆጣሪና የፈንጂ ማምረቻ ፋብሪካዎች ያጠቃልላል። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ኮሎኔል ሃድጉ ገርብጊርጊስና ሜጀር ዘውዱ አለፈ ይባላሉ።
(11) የብረት ፋብሪኬሽን ኢንደስትሪ (Metal Fabrication Industry) ብረታ ብረት የፈጠራ ሥራ ኢንደስትሪ፣
ፋብሪካው በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ-ከተማ ውስጥ ከሜቴክ ዋና መስሪያ ቤት አጠገብ ይገኛል። ፋብሪካው በብረት ፈጠራ ሥራ ዋናዎቹ የግንባታ ማሽነሪዎች፣ የአውቶቡስ አካልና መቃን መሥራት፣ ጀልባ ሥራ፣ ከባድ እቃ ማንሻ መሣሪያ ለፎቅ፣ የግንባታ አሳንሱር፣ የኤሌትሪክ ማከፋፈያ ማማ፣ ተገጣጣሚ ቤቶች ማምረቻ፣እንዲሁም የቅጂና መጫን ምርቶች ያካትታል። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሻንበል ቢቂላ በቃና እና ጌታሁን ገብረ ትንሣይ ይባላሉ።
(12) የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ (Ethiopia Power Engineering Industry (EPEI))
በ2010 እ.ኤ.አ. በሜቴክ ተመሠረተ። ፋብሪካው ከአዲስ አበባ ከተማ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ካንፓኒው በስሩ ሰባት ፋብሪካዎችን ያካትታል። እነሱም የትራንስፎርመር ማምረቻ ፋብሪካ፣ የኤሌትሪክ ሽቦና ቱቦ ማምረቻ፣ አውቶማቲክ የኤሌትሪክ ኃይል ማስተካከያ፣ የኤሌትሪክ ኃይል የሚተላለፍበት/ ስብስቴሽን ጥገናና መለዋወጫ ማምረቻ፣ የፀሃይ ብርሃን ማጠራቀሚያ ባርድ ማምረቻ፣ የሞተርና የጀነሬተር ማምረቻና፣ የሞተር፣ እንዲሁም በፈሳሽ ወይም በዓየር የሚሽከረከር/ተርባይን ሞተር ማምረቻ ፋብሪካዎች ናቸው። በአሁኑ ግዜ ጀነራል ማናጀሩ ሜጀር አስፋ ዩሃንስና ሻንበል ዘመድኩን ይባላሉ።
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ የኤሌትሪክ ሽቦና ቱቦ ማምረቻ ፋብሪካ እንዲሁም ከ400 KV እና 500 KV ከፍተኛ ቮልቴጅ የኤሌትሪክ መስመር ማስተላለፊያ ተሸካሚዎች ( high-voltage electricity- transmission cables,) በሁለት መቶ ሚሊዩን ብር ወጭ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብና ለግልገል ጊቤ ሦስት ፕሮጀክቶች ሥራ ተሠጥቶታል።
ፋብሪካውም ከአዲስ አበባ ከተማ 70 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሞጆ ከተማ ውስጥ ተገንብቶል። “The Ethiopian Power Engineering Industry inaugurated a wire and cable factory which is one of its eight factories built in the Modjo town at a cost of 200 million Birr to produce electric cables that can carry 400 and 500 KV, especially for the power transmission of the Grand Renaissance and Gibe III dams.”
በአሁኑ ግዜ በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በመከላከያ ሚኒስትር ሥር የሚገኘው፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ከሰባ አምስት እስከ መቶ ፋብሪካዎች በላይ በስሩ ያሰባሰበ ድርጅት ሲሆን የፋብሪካዋቹ፣ የሥራ ዘርፎች፣ የካፒታላቸው መጠን፣ የግብር አከፋፈላቸው፣ የስም ዝርዝራቸውን፣ የሚገኙበት ቦታ፣ ጀነራል ማናጀራቸው፣ የኦዲት ሪፖርታቸው ለህዝብ ይፋ አይደሉም። የመንግስት ሞኖፖሊ ማለት ለህገ-መንግስቱና ለህግ ተገዥ ያለመሆን ስርዓት በመገንባት ላይ ይገኛሉ።
በዚህም ምክንያት በብዙ ታዳጊ አገሮች የፕራይቤታይዜሽን ሽግግር በብቃት፣ በእኩልነትና በግልፅነት ለማካሄድ አስፈላጊው ግዜና ጥናት ባለመካሄዱ የተኮላሸ ለመሆን በቅቷል። በታዳጊ አገሮች ውስጥ የገበያ ውድድር ያለመኖር፣ የመዋለ-ንዋይ ፍሰት ደካማነት፣ የፋይናንሻል ሃብት እጥረትና የግሉ ዘርፍ በኢኮኖሚው ውስጥ የሚጫወተው ሚና ደካማነት ወዘተ ተደማምሮበት የፕራይቬታይዜሽን ሽግግር የተጨናገፈ ለመሆን በቅቷል። በኢትዮጵያ የፕራይቬታይዜሽን ሽግግርና ሂደት በቂ በሆነ የአገር ውስጥና የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ባለመሳተፋቸው ምክንያት አብዛኛዎቹ የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና ንብረቶች ባለቤትነትን ወደ ኢፈርት፣ ሜቴክና ሜድሮክ የመሳሰሉ ካንፓኒዎችና ንብረትነት ማዘዋወራቸው የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች ያገለለና ያለ ገበያ ውድድር ለጥቂቶች ያለዋጋቸው የተቸበቸቡ የህዝብ ንብረቶች መሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል።
በኢትዮጵያ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ዓላማዎች፣ እንደ አዋጅ ቁጥር 146/1998 አንቀፅ 3 መሠረት ዋና ዓላማዎች ውስጥ፣
መንግስት ለሚያከናውነው የምጣኔ ሃብት እድገት የገቢ ምንጭ በመሆን የገንዘብ ፍሰቱን በቀጣይነትና በዘላቂነት ማጠናከር፣
የመንግስት በሃገሪቱ ኢካኖሚ እድገት ሚናና ተሳታፊነት እንዲጎለብት በማድረግ ትልቅ አስተዋፅዖ ማድረግ፣
እንዲሁም መንግስት የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን የግል ዘርፉን ኢኮኖሚ ለማበረታታትና ለማስፋፋት የሚል ቢሆንም ከደርግ ወደ ህወሃት መንግስትዊ ሞኖፖሊነት የተሸጋገረ ኃብት ለመሆን በቅቷል።
በኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ከ1996 እስከ ዲሴንበር 2000 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 166 የመንግስት ኮርፖሬሽኖችንና ንብረቶች ወደ ግሉ ዘርፍ ንብረትነት ተዘዋውረዋል። ከነዚህም ውስጥ 130ዎቹ በሜድሮክና ግለሰቦች ተገዝተዋል። ከነዚህ ውስጥም 45ቱ ለኢህአዲግ አዲስ ፋና ድርጅት ሠራተኞች ተሸጠዋል። 10 በቢዝነስ ድርጅቶች፣ 36 ኢንተርፕራይዝ በመንግስትና መንግስታዊ በሆኑ ድርጅቶች በመከላከያ ሚኒስትር ስር ለተቋቋመው ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ተሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ በግሉ ዘርፍ፣ በብረታ ብረትና ፋብሪካዎች ግንባታ ኢንቨስትመንት ላይ የተሳተፉ ከሃያ አራት በላይ ባለሃብቶችን በውጭ ምንዛሪ ችግር ይሰቃያሉ። በኤሌትሪክ ኃይል እጥረት (63 በመቶ)፣ ከውጭ በሚገባ ተመሳሳይ ምርቶች ውድድር (61 በመቶ)፣ ዝቅተኛ የሰው ሃብት ልማት/የእውቀት ደረጃ መኖር (70 በመቶ)፣ የምርምርና የልማት ጥናቶች ያለመኖር (80 በመቶ)፣ ከሣይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ትብብርና ድጋፍ ማጣት እዲሁም የምርት አቅርቦታቸውን ለሃገር ውስጥ የግንባታ ዘርፍ ለማቅረብ ያለ ራዕይና የቴክኖሎጂ ሽግግር/ ልውውጥ አለመኖር በብረታ ብረት ኢንደስትሪ የግል ዘርፉ የተሰማሩ ባለሃብቶችን ለኪሳራ የዳረጋቸው አንካኳር አንካኳሮቹ ችግሮች እንደሆኑ ጥናቱ አመላክቶል። ለዚህ ይመስላል የግል ባለሃብቶቹ “ትልቁ ዓሣ ትንንሾቹን ዓሣዎች ዋጦቸው” በማለት ምሬታቸውን የሚገልፁት። የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሰው አልባ ድሮውን (ሰው የሌለው የጦር አውሮፕላን ሰራን ብለው) በኢትጵጵያ ቴሌቪዝን የውሸት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ይታወቃሉ። ሜቴክ አውቶብስ፣ መኪናና ትራክተር ከመገጣጠም ያለፈ ይሄ ነው የተባለ ሥራ አልሰራም!!! የድሮውን ሥራ ቀርቶብን የገበሬውን የእርሻ መሣሪያዎች ብታሻሸሉ ምን ያህል በተመሰገናችሁ ነበር!!!
“Ethiopia produces first military drone aircraft:-February 14, 2013 (ADDIS ABABA) – An Ethiopian military source has told Sudan Tribune that the country has built the first unmanned aerial vehicle (UAV) or drone which could be used for multiple purposes. After undergoing testing, the locally made drones, have demonstrated their capability of performing a number of militarily and civilian applications, according to the source.”
ሜቴክ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስተሮች የሚሰሩትን ስራ በመንጠቅ ብዙዎቹን ከንግድ ዓለም በማሰወጣታቸው ነው በግሉ ዘርፍ የተሰማሩት የሃገሪቱ ነጋዴዎች የሚመሰክሩት። አንድ ግዜ ሜቴክ ለፎቅ ግንባታ የሚውል የተለያዩ ፌሮ ብረቶች አስራ ሦስት ቢሊዩን ብር የሚገመት የብረት ምርት ክምችት፣ አምርቶ አልሸጥ ብሎት ለመንግስት አቤቱታ ማሰማቱ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው። ሜቴክ የወታደራዊ ምርቶችን ከማምረት አልፎ ለምን የሲቪሉ የግል ባለሃብቶች የተሰማሩበትን የማኑፋክቸሪንግ የንግድ ስራ ላይ ይሻማል!!! አባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ! ማለት ይሄ አይደለም። የህወሃት የመከላከያ የጦር አበጋዞች ከሜቴክ በሙስና በዘረፉት ገንዘብ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ፎቆች እንደገነቡ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ከህዝብ የሚሰወር ምንም ሚስጥር የለም እውነትና ንጋት እያደር ይታወቃል።
በህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት በመከላከያ ሚኒስትር ሥር የሚገኘው፣ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ብኢኮ) ከግሉ ዘርፍ ኢንቨስተሮች ጋር ያለ ነፃ የገበያ ውድድር፣ ከመንግስት ያለአንዳች ጨረታና ውድድር የሚሰጠው በብዙ ቢሊዩን ብር ፕሮጀክቶች ሥራ ያገኛሉ። እነዚህ መንግስታዊ የንግድ ድርጅቶች ባላቸው የፖለቲካ ሥልጣንና መንግስታዊ ወገንተኝነት ሁሉ ነገር አለጋ በአልጋ እንደሚሆንላቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። ለዚህ ነው የግሉ ዘርፍ በሚፈፀምበት አድሎ የሚቀጭጨውና የነፃ ንግዱ ውድድር ፍትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት ለኪሳራ የሚዳረገው። በዓለማችን በሚገኙ ሃገራቶች የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ መሠረተ ልማት ግንባታ፣ የስካኳር ፋብሪካዎች ግንባታና የብረታብረት ኢንደስትሪዎች ግንባታ በግሉ ዘርፍ ኢንቨስተሮች ሃብትና እውቀት የሚሰሩ ፕሮጀክቶች እንደሆኑ ይታወቃል። በኢትዮጵያ ግን እነዚህ ዘርፎች በመንግስታዊ ዘርፍ ቁጥጥር ስር በሆኑ ድርጅቶች እንዲሰሩ በማድረግ የግሉን ዘርፍ እንዳይሰራ ያገለለ ሆኖ እናገኛለን። ይህም ባይተገበር በጋራ በመንግስትና በግሉ ዘርፎች ቢሰራ ይመረጣል። ለዚህ ነው ሜቴክ የመሳሰሉት በመንግስታዊ ሞኖፖሊነት የህዳሴው ግድብ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽንና፣ የኢትዮጵያ ስካኳር ኮርፖሬሽን፣ ፕሮጀክቶች ሥራን ጠቅሎ እንዲሰራ መደረጉ ይታወቃል። የህወሃት መንግስት ለመከላከያ ሚኒስቴር፣ ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ከሠጣቸው ፕሮጀክቶች መካከል በጥቂቱ ቀጥለን በዝርዝር እናቀርባለን፡-
(1)ሜቴክ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ (Ethiopia Power Engineering Industry (EPEI))
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የፕሮጀክት ሥራ ላይ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራ የአምስት ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር የኮንትራት ሥራ መቀመጫውን ፓሪስ ካደረገው የአልሰም (Alstom SA) ካንፓኒ ስምንት ተርባይንስና ጀነሬተሮች በ250 ሚሊዩን ዩሮ (333 ሚሊዩን ዩኤስ ዶላር) በማቅረብ ተስማምቶል። የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ኢንጅነሪንግ ኢንደስትሪ የድለላ ሥራ በማከናወን ከአልሰም ኮሚሽን ያገኛል። እንዲሁም መሠረቱን አሜሪካ ካደረገው ሶላር ፓኔል ማኑፋክቸር ስፓየር ኮርፖሬሽን (Spire Corp.) እና ከቻይና ፖሊ ግሩፕ ኮርፖሬሽን (China Poly Group Corp.) ጋር የኢንጅነሪንግና የማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክቶች ሥራን በማከናወንና ከነዚህ ድርጅቶች ሜቴክ በድለላ ሥራ ኮሚሽን ቦጭቆ፣ የኢትዩጵያ ህዝብ ይቦጭቃል።
“The Ethiopian Electric Power Corp. contracted METEC to build the electro-mechanical works for the $5 billion Grand Ethiopian Renaissance Dam on the Blue Nile River in partnership with Alstom. The Paris-based company will provide eight turbines and generators for 250 million euros ($333 million) to METEC and commission the plant.”
“METEC awarded Alstom a €250m ($326m) worth contract in January 2013, to supply eight 375 MW Francis turbines and generators for phase 1 of the Grand Renaissance hydro power project. Alstom will also provide engineering and power plant commissioning services as part of the contract. Tratos has been awarded a contract by Salini to provide low-and high-voltage cables for the project….
Two underground power houses will be situated on the river’s right and left banks downstream of the main dam. The power houses will be equipped with ten and five 375MW Francis turbine units respectively. A 500kV double bus-bar switchyard will be built 1.4km downstream of the main dam to transmit the output of the hydroelectric plant.”… “It is the main electromechanical and hydraulics steel structure contractor of the Renaissance Dam. The Corporation has provided steel products used for the work of diverting the course of the river, which was officially commissioned on May 28.”
(2) ሜቴክ ለፕራይቬታይዜሽንና መንግስታዊ ኢንተርፕራይዝ ተቆጣጣሪ ድርጅት ( Privatization and Public Enterprises Supervising Agency) ጋር የ2.8 ቢሊዩን ብር የከሰል ፎስፌት ማዳበሪያ ኮንፕሌክስ ፕሮጀክት (Coal Phosphate Fertilizer Complex project) በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ፋብሪካውም ከአዲስ አበባ ከተማ 600 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በኦሮሚያ ክልል በኢሉባቡር ዞን ውስጥ በመገንባት ላይ ይገኛል። የህወሃት መንግስት 2.8 ቢሊዩን ብር ሁለት የማዳበሪያ ፋብሪካዎች ለመገንባት አቅዶል። ሜቴክ የሚገነባቸው አምስቱ የዳፕና ሦስቱ ዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካዎች ሲሆኑ 2013/14 መጨረሻ ተጠናቀው ያልቃሉ ተብሎ ይገመታል። ስምምነቱን የተፈራረሙት የፕራይቬታይዜሽን በየነ ገብረመስቀልና የሜቴክ ኮነሬል ሙሉ ወልደገብርኤል ሲሆኑ የኢንቨስትመንት ወጭው 55 ቢሊዩን ብር እንደሆነ ከድረ-ገፁ መረዳት ተችሏል። ነገር ግን ፕራይቬታይዜሽን መንግስታዊ ኢንተርፕራይዝ ተቆጣጣሪ ድርጅት “የመንግስት የልማት ድርጅቶችን” ወደ ግሉ ዘርፍ ማስተላለፍ እንጂ ይሄን ዓይነት የግንባታ ሥራ እንዲሰራና እንዲያስፋፋ ስልጣን በአዋጅ አልተሠጠውም። ፕራይቬታይዜሽን ድርጅት በሙስና የዘቀጠ ድርጅት ሲሆን አንድ ቀን በሰራው ስራ ይጠየቅበታል። የማዳበሪያ ፋብሪካው ሲጠናቀቅ በሜቴክ ቅርብ ግዜ በተቆቆመው “የኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን” እንደሚዘዋወር ውስጥ አዋቂዎች አረጋግጠዋል።
በ2014 የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የግብርና ግብዓቶች አቅርቦት ኢንተርፕራይዝ (Agricultural Input Supply Enterprise) በማለት ያቆቆመው መንግስታዊ ድርጅት፣ 900,000 ሽህ ቶን ፈርትላይዘር፣ 375,000 ቶን ዩሪያ (381.5 ዩኤስ ዶለር) ና 521,000 ቶን ኤንፒእስ NPS (412ዩኤስ ዶለር) ዋጋ ፈርትላይዘር ለመግዛት ጫረታ ስጥተዋል። ሃገሪቱ ለማዳበሪያ በአመት 357,714,500 ዩኤስ ዶለር (14,308,580,000 ቢሊዩን ብር) የውጭ ምንዛሪ ታወጣለች። በግ.ቀ.ኃ.ሥ ዘመን አንስተው በኢትዮጵያ የሚቼል ኮትስ ካንፓኒ ባለቤት አቶ ገብረየስ ቤኛ በሃገሪቱ የፈርትላይዘር ምርቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ በማስተዋወቅና አስገብቶ በማከፋፈል ይታወቁ ነበር። እኝህን የግል ባለሃብትን ከስራቸው ነቅለው፣ የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት ገበሬውን የራሳቸው ጭሰኛ በማድረግ ማዳበሪያ የማከፋፈሉን ስራ መንግስታዊ ድርጅትና የፖለቲካ ድርጅቶች ተረከቡት። የሃገራችን እድገት የግሉን ዘርፍ ስራ በግፍ በመንጠቅ ለመንግስታዊ ዘርፍ በማስተላለፍ መንግስታዊ ሞኖፖሊን ማስፋፋት ነው።
“MetEC is also building Yayu Coal Phosphate Fertilizer Complex project, 600km west of the capital in the Illubabor Zone, Oromia Regional State. It is one of the two fertilizer factories that the federal government wants built at a total cost of 2.8 billion Birr. … Michael said. The fertilizer project will be transferred to the newly formed Chemical Industry Corp. when it’s finished.”
“Moreover, the Ethiopia ‘Metal and Engineering Corporation’ (METEC), a government engineering company, is in advanced stages of completing eight fertilizer producing factories, five of which will be producing Diammonium Phosphate DAP and three for Urea and Ethiopia is targeting reaching production stage by the 2013/14 cropping season.”
“MetEC is also building a Coal Phosphate Fertilizer Complex in the Oromia Regional state and is the main contractor for the Sugar Corporation, a state-owned enterprise developing cane plantations and building multiple processors across the country at a cost of about USD 5 billion. ”
“Ethiopia has inked a deal facilitating construction of five fertilizer units with an investment of 55 billion birr. Signing of the agreement was done by Beyene Gebre-Meskel, Director General of PPESA and Col. Mulu Wolde- Gabriel Project management Deputy Director with Metal Engineering. According to Col. Mulu, the agreement is to construct five urea and three Dap fertilizer units and one coal factory. Each of the Urea fertilizer factories will have yearly production capacity of 300,000 tons. The Dap factories would facilitate supply of 250,000 tons. The project even includes a plant to supply 1.1 millions tons of phosphate element as input. Beyene said, completion of the construction phase will take around three years with the Urea factories being launched first and the others to be set up as per a schedule.”
(3) ሜቴክ ለኢትዩጵያ ስካኳር ኮርፖሬሽን፣
አስር የሸንኮራ አገዳ እርሻዎችና የስካኳር ፋብሪካዎች ፕሮጀክቶች ሥራን በአምስት ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ ነው ቢባልም ሃገሪቶ ከ500 ሚሊዩን ዶለር በላይ በማውጣት ከውጭ የስካኳር ምርት በማስገባት ላይ ትገኛለች።
“Metal Engineering is currently engaged in significant projects such as sugar plants. METEC is the main contractor for the Sugar Corp., a government enterprise that’s building 10 cane plantations and processors nationwide at a cost of about $5 billion”
“Established a year ago and entrusted with several government projects worth billions of Birr, MetEC, run by a high ranking military officer, Kinfu Dagnew (BGen), involves several projects including the electromechanical work of the Grand Ethiopian Renaissance Dam and the erection of a turnkey fertilizer and 10 sugar plants in various parts of the country.”
(4) ሜቴክ የብሸፍቱ አውቶሞቲቨ ኢንደስትሪ ፋብሪካ
የህዝብ ትራንስፖርት አውቶብሶች፣ የከተማ ውስጥ አውቶብሶች፣ የጭነት መኪናዎች፣ ፒክ አፕ መኪናዎችና ሲዩቪ መኪኖች ይገጣጥማል። ፋብሪካው ሃያ ሚሊዩን ብር (1.1 ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር) ትርፍ በዓመት እንደሚያገኝ ሚካኤል ደስታ የካንፓኒው ቃል አቀባይ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በአምስቱ አመት እቅድ 2010/11 እስከ 2015እኤአ 569 ቢሊዩን ብር ለሜጋ ፕሮጀክቶች የመገንቢያ ወጭ ባጀት መያዞ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ውስጥ መንግስት ለመንግስታዊ ኢንተርፕራይዞች ዘርፍ ያለ ጨረታ የሚሰጠውን የፕሮጀክቶች ብዛት ማስተዋሉ ይጠቅማል፡፡
“Similarly, the Corporation also inaugurated a heavy truck assembly factory, which is operating under the Bishoftu Automotive Industry. …Some of the company’s budding industries, like vehicle-assembly and engineering businesses, may generate more than 20 billion birr ($1.1 billion) of revenue a year, spokesman Michael Desta said in an interview.”
“The government is in the midst of a five-year plan in which it’s spending 569 billion birr until 2015 on projects including the $5 billion Grand Ethiopian Renaissance Dam, which would be the site of Africa’s biggest hydropower plant. ”
“Former Prime Minister Meles Zenawi, who ruled Ethiopia for 21 years before he died in August, may have created METEC to give the military a “stake” in the economy, said Merkeb. “Now the military will always defend the system whatsoever,” he said in an e-mailed response to questions on Feb. 6. ”
Ethiopian Military-Run Corporation Seeks More Foreign Partners..By William Davison 2013-02-18T04:03:30Z Vehicle Manufacturing ,A METEC arms factory was opened the same day, it said on its website.
Poly Technologies Plc, part of the Beijing-based China Poly Group, is building truck-assembly plants in Modjo and Bishoftu for METEC, Xinhua reported on Sept. 27.
To contact the reporter on this story: William Davison in Addis Ababa at
wdavison3@bloomberg.net
,
asguazzin@bloomberg.net
(5) ሜቴክ የኢትዮጵያ ሪቬራ ኢንተርናሽናል ሆቴል (Ethiopian Riviera International Hotel)
ባለ ሦስት ኮኮብ ደረጃ ያለውን የአቶ አለም ፍፁም ንብረት የነበረውን እንዲሁም ፒቪሲና ፕላስቲክ ማኑፋክቸሪንግ ፋብሪካ በ140 ሚሊዩን ብር ለመግዛት ስምምነት አድርጎል። በተመሳሳይ ሜቴክ በአዲስ አበባ የሚገኘውን ኢምፔሪያል ሆቴል በ60 ሚሊዩን ብር ገዝቶ ሆቴሉን የእንግዳ መቀበያ ለማድረግ አቅዶል።
“The Metal and Engineering Corporation concluded a deal to acquire the Ethiopian Riviera International Hotel, primarily owned by Alem Fitsum. The deal includes the three star hotel and a PVC and plastics manufacturing plant located behind the hotel. The deal was struck for approximately 140 million birr with negotiation still going on and handover expected in the coming weeks according to sources. MetEc aims to utilize the hotel to house guests that will stay for more than a month saving it a lot of money according to an unofficial source.”
“It is to be remembered that Metal and Engineering Corporation reached an agreement with Access for the sale of Imperial Hotel in February. The agreement is estimated to be worth 60 million birr.MetEC will transform the property into a guesthouse to host its international associates and it is a yet not known whether the guesthouse will be open for general service according to an anonymous source with the corporation.”
(6) ሜቴክ ከስፓየር ኮርፖሬሽን ፎቶቮልቲክ መሣሪያ 20 ሜጋዋት የሚያመነጭ ሶላር አሴንብሊ ላይን በእርዳታ አግኝቶል። የኢትዮጵያ መንግስት በሚቀጥሉት አምስት አመታት ከፀሐይ ኃይል 20 ሜጋዋት ለማመንጨት ዕቅድ አውጥቶል። የኢትዮጵያ ሕዝብ 80 በመቶው የመብራት አገልግሎት እንደማያገኝ ተረጋግጦል።
Ethiopia’s Metals and Engineering Corporation to Receive Solar Assembly Line,Published by Sodere on April 12, 2012 BEDFORD, Mass., Apr 12, 2012 (BUSINESS WIRE) — Spire Corporation SPIR -0.95% , a global company providing solar photovoltaic equipment and systems announced today that it will provide a 20 megawatt (“MW”) Photovoltaic (“PV”) module turnkey assembly line to the collaboration of SKY Energy International, Inc. (“SKY”) located in Florida and Metals and Engineering Corporation (“METEC”) located in Ethiopia.
The module assembly line will be established in Addis Ababa, Ethiopia. The facility will be the first state-of-the-art module manufacturing line in Ethiopia. The Ethiopian Government has announced its goal to have 20% of its power capacity coming from solar energy within the next five (5) years.“We are pleased to support SKY and METEC to bring solar to Ethiopia. Ethiopia is a nation where 80% of the population presently does not have access to electricity,” said Roger G. Little, Chairman and CEO of Spire Corporation. SOURCE
www.spirecorp.com
.
(7) ሜቴክ ከኢትዩጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ድርጅት ጋር የአናሎግ ኤሌትሪክ ሜትርን በአዲስ ፈጣን አውቶማቲክ ዲጂታል የኤሌትሪክ ሜትር (የኤሌትሪክ ቆጣሪው የኃይል ፍጆታውንና ዋጋ ተምኖ ለድርጅቱ የሚያሳውቅ ) ለመስራት የ9 ቢሊዩን ብር ኮንትራት ሥራ ለመስራት ተስማምቶ መስራት ስላቃተው ጨረታው ተሰርዞል። ከኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ድርጅት ከህንድ ካንፓኒ ጋር በ27 ሚሊዩን ዶላር ሥራውን በኮንትራት ሠጥቶል።
As part of its expansion, the Corporation has also agreed to replace the electric meters operated by the Ethiopian Electric Power Corporation. The project is valued at nine billion birr and is expected to replace electric meters with new ‘smart’ meters. The new ‘smart’ digital meters are expected to automatically register electric consumption and report back to EEPCo without requiring manual reading like the analog meters currently being used. However, MetEC has failed to deliver the commitment it owes to EEPCo.
As a result, the latter had to make an urgent and alternative deal with an Indian company. This also cost EEPCo more than USD 27 million foreign exchange. Hence, critics claim that these transformers could have been done by other local companies if MetEC hadn’t muscled them down.It is to be remembered that the Ethiopian Electric Power Corporation is requiring all factories in Ethiopia to install devices that guarantee efficient use of power. The Metal and Engineering Corporation has snatched the responsibility to produce the devices known as power factor correctors. The efficiency devices will be made available to all factories eventually on a one-year interest-free credit arrangement, according to EEPCo Officials.The efficiency devices are expected to adjust the difference between real power and apparent power in the use of electricity to a ratio of one. However, still, private companies face sort of a setback from the device being manufactured by MetEC, which forces them to pay the electric bill, including the power leakage due to inefficient power meter.
(8) The increasingly fragile Ethio-Djibouti railway line has temporarily halted the service stretching from Dire Dawa to Djibouti, The Reporter has learnt. Continue read→THE ETHIOPIA OBSERVATORY
Archive | metal and engineering corporation (MEtEC) Dispute with MEtEC halts existing railway service operations: Why is MEtEC stone in everyone’s shoe?
(9) MetEc to produce 100MW electric power from waste ..June 9, 2014 Addis Ababa,
Metal and Engineering Corporation (MetEc) has signed a memorandum of understanding with the Addis Ababa city administration and the Ethiopian Electric Power Service to produce 100 MW of electric power from Addis Ababa’s waste. MetEc has also signed an agreement last week with the Canadian company that provides the technology for generating electric power from waste. MetEc is expected to begin operation next month once it finalized the agreement with the Canadian company. The waste power generators will be located at the Akaki-Kaliti and Bole-Arabsa solid waste sites.The project’s 75% power will be generated from Addis Ababa’s solid waste and the remaining 25% is known to be from the city’s liquid waste. MetEc is preparing to receive fourteen hectares of land for the project. The finance source for the project will be provided by the Canadian company. The amount of electric power generated depends on the amount of waste available. Once the project is finalized and when power generation is started, Ethiopian Electric Power Service will issue the payment for the project through MetEc. It is remembered that a British company named Harvard had began operation to generate electric power from the waste located at the Repi area of Addis. source: Reporter
(10) Metec to buy 10 industries from Asia,
Monday, 03 June 2013:-Metal and Engineering Corporation (MetEc), a state-owned enterprise is in the process of acquiring ten metal and metal-related industries from Asia. The corporation, which is involved in several mega governmental projects, is establishing large metal industries in the country, developing a range of plants in the mechanical sector, to help boost the country’s development. Sources at the corporation told Capital that MetEc is scheduled to establish several metal industries that shall feed major metal projects the corporation is engaged in. The corporation is currently in the process of purchasing 10 metal and metal-related industries already set up abroad and will arrange for their transfer to Ethiopia in order to set them up in the different regions in the country. According to these sources, corporation officials have been negotiating and making deals for nearly a year to buy up the above-mentioned industries in Asia for relocation. And even though the deals haven’t been finalised yet, it was indicated that MetEc plans to buy and relocate ten industries from China and India. According to experts, while these industries have been manufacturing products for the past several years in their respective countries, the corporation made the decision to purchase and transfer them here, because it would be less costly than establishing similar new industries. Our sources explained that the metal factories included in the purchase shall mainly be engaged in the production of metal spare parts, bolts and nuts and the likes. MetEc is scheduled to undertake crucial projects in the coming years as part of the five-year Growth and Transformation Plan (GTP) and has secured a huge budget to expand its capacity in terms of quality and quantity of production. The corporation has hence become one of the major government corporations spending billions of birr on different new and expansion projects.
(11) Defense’s MetEC gives delicious 1st class contract to MIDROC, Ethiopia’s tyre monopoly 26 Jun
When the newly-invigorated parliament after the death of Meles Zenawi pointed out the weaknesses and bad practices of the Ethiopian Investments and Privatization Agency, its Director-General Beyene Gebremeskel, whose agency has been known as MIDORC’s buddy, was the first to protest, as reported by the Reporter. Whose interests should the country serve, some powerful politicians or that of corporate [deleted] up? It is time Ethiopia stopped to carefully think how it should best serve its interests as a nation and the interests of its people! It is time to shake off corrupt senior officials facilitating from within corrupt practices that with every passing year is pulling down Ethiopia into becoming a failed state! Signed market and technical assistance agreement with MetEC Horizon Addis Tyre is to produce 22 different sizes tyres for the various vehicles the Metal and Engineering Corporation (MetEC) produces. Horizon Addis, the sole manufacturer of tyres in the country, has been supplying a limited amount of tyres for the market and has not been able to cope with the public’s demand in the last 40 years. This company has today a new market and will also receive technical assistance from its latest customer, according to the cooperation agreement it signed with MetEC on June 18. … Horizon is planning to produce tyres in 22 different sizes in the current fiscal year. According to the General Manager, all these sizes are presently imported from abroad. He said this move is a manifestation of Horizon’s commitment to the nation.
“In 2011, the company was again renamed; this time to Horizon Addis Tyre when Horizon Plantation Plc, owned by the Ethiopian-born Saudi billionaire, Sheik Mohammed Hussein Ali Al Amoudi, took over the shares of Matador. Twenty nine percent of Horizon is still owned by the government. Established in 2010 by the Council of Ministers, MetEC is a governmental institution set up to realize the government’s Growth and Transformation Plan (GTP) and accelerate the ongoing transition of the country into industrialization. The corporation comprises 15 semi- autonomous, and integrated manufacturing companies that are operating in more than nine different sectors.›› Source: Capital New Tyres Skid Into the Market,Al-Amoudi’s Horizon Acquires Matador-ATC’s 69pc for 18m
(12) Ethiopia: MetEC to Assemble Polish Tractors, September 26, 2014 –
Based on a knocked-down export agreement concluded between Ethiopian Metals and Engineering Corporation MetEC and Ursus SA, Polish agriculture equipment producer, MetEC is prepared to take delivery of the first 1,500 tractors from the latter. The Ethiopian Metals and Engineering Corporation (MetEC) is prepared to receive the delivery of the first of 1500 polish tractors produced by the oldest polish agricultural equipment brand, Ursus SA, based on a knocked-down export contract worth USD 90 million signed exactly a year ago.
(13) ሜቴክ በአዲስ አበባ ከተማ 116 ተንቀሳቃሽ መፀዳጃ/ሽንት ቤቶች ለመስራት ከአዲስ አበባ የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ባለስልጣን ኮንትራት ተሰጥቶታል። የአንዱ መፀዳጃ/ ሽንት ቤት መቶ ሽህ ብር ወጭ ጠቅላላውን 11,600,000 ሚሊዩን ብር እንደሚሰራ ተዋውሏል። ከድሮውን/ከሰው አልባ አይሮፕላን ወደ መፀዳጃ ሽንት ቤት ሥራ!!! ንቧ የግሉ ዘርፍ ምን ሰርቶ ይብላ ዝንብ ሆናችሁበት እንኳ?
Ethiopia: MetEC to Deliver 116 Mobile Toilets to Addis Ababa,September 24, 2014
MetEC is going to deliver 116 three square meter mobile toilets to the Addis Ababa Water and Sewarage Authority (AAWSA). The mobile toilets costed near 100,000 Birr each.
(14) ህብረት ማኑፋክቸሪንግና የማሸን ግንባታ ኢንደስትሪ በ350 ሚሊዩን ብር ወጭ የመኪና የፍሬን ሸራ በአምስት ወራቶች ውስጥ ገንብቶ ለማስረከብ ተስማምቶል፡፡
Ethiopia: Break Rubber Factory to Start Production in Five Months,September 19, 2014
Ethiopia’s first break rubber factory, Hibret Manufacturing and Machinery Fabrication, which cost 350 Million Birr is going to start production in five months time.
(15) ሜቴክ ከኢትዩጵያ መርከብ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ሁለት አሮጌ መርከቦች ‹አባይ ወንዝ›ና ‹አብዬት› በመባል የሚታወቁትን ገዝቶ በመጠገን የአገር ውስጥና የባህር ማዶ መርከበኞች ቀጥረው የሜቴክን እቃዎች ለማጎጎዝ የሜቴክ ጀነራል ማናጀር ብርጌደር ጀነራል ክንፈ ዳኘው አቅደው ነበር፡፡ ብርጌደር ጀነራል ክንፈ የኢትዩጵያ ህግ ከኢትዩጵያ መርከብ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ድርጅት ሌላ የመርከብ አገልግሎት መስጠት እንደማይችል አልተረዱም ነበር? በህጉ ምክንያት መርከቦቹን ለመሸጥ በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ ብርጌደር ጀነራል ክንፈ የቄሳርን ለቄሳር፣የመከላከያን ለመከላከያ፣የባህሩን ለባህርተኛ ነው ህጉ የደነገገው፡፡ የመንግስታዊው ዘርፍ(ሜቴክ) የግሉን ዘርፍ ሥራ መስራት አይገባውም፣ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ይገድለዋል ነው የሚሉት የኢኮኖሚ አጥኝዎች፡፡
“The Metal and Engineering Corporation (MetEc) is going to sell back the two vessels, ‘Abay Wonz’ and ‘Abyot’, that it bought last year to use as scrap metal from the Ethiopian Shipping and Logistics Service Enterprise (ESLSE). Brigadier General Kinfe Dagnew, Director General of MetEc, told Capital that the corporation changed its plans after experts confirmed that the vessels are still operable. “Now we are planning to sell the vessels after repairing them,” he said. Kinfe said that the corporation has sent the two vessels to Dubai, UAE for repair works. “Repair on one of the two vessels have already been completed,” the general said. He also indicated that local and international crew have already been hired to operate the vessels. MetEc initially planned to use the vessels to transport its own cargo before using them as scrap metal. These plans had to be abandoned, as Ethiopian law does not allow any other ship operator as the ESLSE is the sole entity that can own and operate ships. MetEc, which is involved in a number of large government projects, is also busy establishing ten metal factories around the country, which it is in the process of relocating the factories it bought from Asia.”
ማጠቃለያ፤
የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ አማካኝነት ወደ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ያለአንዳች ብር ክፍያ የተዘዋወሩ ንብረቶችና የህዝብ ኃብት ዘረፋን በቀላሉ መረዳት ይቻላል። በዚህም ምክንያት በኢትዮጵያ የተካሄደው የፕራይቬታይዜሽን ሽግግር የብዙ የሰው ሃይል (ሠራተኞች) ቅነሳን ያሰከተለ፣ ምርታማነትን የቀነሰ፣ ተጨማሪ ኢንቨስትመንትን ያልጨመረ፣ መሆኑ በጥልቅ ጥናቶች ተረጋግጦል። የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ውድቀትና የወደፊት እ